Maasiai
~ መዕሣይ: Work
of Jehovah / EBD, The name “Maasiai” means the defense, or
strength, or trust of the Lord / SBD, (1 ዜና 9:12)
The root
words for ‘Maasiai’ are ‘Mse’ (ምሰ) and ‘Yah’ (ያህ) ፥ the
meaning is ‘work of Jehovah’/ Ibid.
A
priest who after the return from Babylon dwelt in Jerusalem, “...the son of Malchijah, and Maasiai the son of Adiel, the ...” (1 Chr 9:12)
----------------------------------------------------------------------------------------------------
መዕሤያ ~Maaseiah: መሲ ያህ፣ መሳያህ፣ የአምልክ መድሐኒት፣ የጌታ መፍትሄ ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- መሕሤያ፣ መዕሣይ]
----------------------------------------------------------------------------------------------------
መዕሤያ ~Maaseiah: መሲ ያህ፣ መሳያህ፣ የአምልክ መድሐኒት፣ የጌታ መፍትሄ ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- መሕሤያ፣ መዕሣይ]
‘መሲሕ’ እና ‘ያህ’(ያህዌ፣ ህያው) ከሚሉት ሁለት ስሞች ተጣምሮ የተመሠረተ ስም ነው።
በዚህ ስም የሚታወቁ አሥራ ዘጠኝ ሰዎች አሉ።
1.
በንጉሥ ዳዊት ትዕዛዝ፥ በናያስ በመሰንቆ ምሥጢር ነገር ያዜሙ ከነበር፥ ከሌዋውያን
በሁለተኛ ተራ የሆነው፥
“...መዕሤያን፥ መቲትያን፥ ኤሊፍሌሁን፥ ሚቅንያን፥ በረኞችንም ዖቤድኤዶምንና ይዒኤልን አቆሙ።” (1 ዜና 15:18፣
20)
2.
የካህኑ የኢዮሴዴቅ ልጅ፣ የኢያሱ ልጅ፥ በግዞት ሲኖሩ፣ የሌላ አገር ሴቶችን ካገቡ የእስራኤል ካህናት አንዱ፥ መዕሤያ፥
(ዕዝ 10:18)
3.
ካህኑ የካሪም ልጅ፥
(ዕዝ 10:21)
4.
ካህኑ የፋስኩር ልጅ፥ መዕሤያ፥ (ዕዝ 10:22)
5.
የፈሐት
ሞዓብ ልጅ፥ መዕሤያ፥ (ዕዝ 10:30)
6.
የዓዛርያስ አባት፣ የሐናንያ
ልጅ፥ መዕሤያ፥ (ነህ3:23)
7.
ዕዝራ የህጉን መጽሐፍ ሲያነብ
በጎኑ ከቆሙት
አንዱ፥ መዕሤያ፥ (ነህ 8:4)
8.
ዕዝራ የህጉን መጽሐፍ ሲያነብ
በጎኑ ከቆሙት
አንዱ ሌዊያዊ፥ መዕሤያ፥ (ነህ 8:7)
9.
ከነህምያ ጋር ቃል ኪዳን
ከተፈራረሙት ወገን አንዱ፥ (ነህ 10:25፣26-27)
10.
የባሮክ
ልጅ መዕሤያ፥ (ነህ 11:5)
11.
የብንያም ወገን፣ የቆላያ አባት፥ የኢቲኤል ልጅ፥ መዕሤያ፥ (ነህ 11:7)
12.
ሌላ ሁለት ካህናት በዚህ ስም ይታወቃሉ፥ “ካህናቱም ኤልያቄም፥ መዕሤያ፥ ሚንያሚን፥ ሚካያ፥ ኤልዮዔናይ፥” ፥ “ዘካርያስ፥ ሐናንያ መለከት ይዘው፥ መዕሤያ፥ ሸማያ፥ አልዓዛር ... ኤጽር ቆምን፦ መዘምራኑም ...” (ነህ 12:41
፣
42)
13.
በነብዩ ኤርሚያስ
የተጠቀሰ፣ የሴዴቅያስ አባት፥ ሐሰተኛ ነብይ፥ (ኤር 29:21)
14.
በዮዳሄ ንግሥና ዘመን የመቶ አለቃ
የነበረው፥ የዓዳያንም ልጅ፥
(2 ዜና23:1)
15.
በዖዝያ ንግሥና ዘመን አለቃ
የነበረ፥ መዕሤያ፥ (2 ዜና 26:11)
16.
በአካዝ
ንግሥና ዘመን፥ የንጉሡ ልጅ፣ በዝክሪ የተገደለ፥ መዕሤያ፥ (2 ዜና 28:7)
17.
የኢየሩሳሌም
አለቃ የነበረ፥ መዕሤያ፥ (2 ዜና 34:8)
18.
በኢዮቄም ዘመነ ንግሥ
አለቃ የነበረ ሌዋያዊው የሰሎም ልጅ፥
(ኤር 35:4)
·
ካህኑ የኔርያ ልጅ፥
መሕሤያ፥ (ኤር 32:12፣ 51:59)
No comments:
Post a Comment