First-born ~ በኩር: (ዘዳ 21፡17) ... [Related term(s):- Becher, Baruch]
Sons enjoyed certain special privileges, “But he shall acknowledge the son of the hated for the firstborn, by giving him a double portion of all that he hath: ...” (Deut 21:17)
-------------------------------------------------------------------------------------------------
በኩር ~First-born: ብኵር፣ የመጀመሪያ ልጅ፣ በኵሬ ማለት ነው።

[ተዛማጅ ስሞች- በኵር፣ በኵሬ፣ ቢክሪ ፣ ቢክሪ፣ ቤኬር፣ ብኵር፣ ብኮራት፣ ቦክሩ]

‘በከረ’ ከሚለው ግስ የተገኘ ስም ነው።
[ከሰው ወይም ከከብት መጀመሪያ የሚወለድ / መቅቃ]
v    የኃይሉ መጀመሪያ፥ “ነገር ግን ከከብቱ ሁለት እጥፍ ለእርሱ በመስጠት ከተጠላችው ሚስት የተወለደው ልጅ በኵር እንደ ሆነ ያስታውቅ። የኃይሉ መጀመሪያ ነውና በኵርነቱ የእርሱ ነው።” (ዘዳ 21፡17)
v    በኢሳው ፋንታ ያዕቆብ በኩር ተብሎ ተጠራ፥ “...ታላቁም ለታናሹ ይገዛል።” (ዘፍ 25:23) ያዕቆብም፦ በመጀመሪያ ብኵርናህን ሽጥልኝ አለው። ... ዔሳው ብኵርናውን አቃለላት።” (34)፣ “... በኵርነቱን እንደ ሸጠ እንደ ዔሳው ለዚህ ...” (ዕብ12:16)
v    የያቆብ ልጅ ሮቤል፥ “ሮቤል፥ አንተ በኵር ልጄና ኃይሌ...” (ዘፍ 49:3) “የእስራኤልም በኵር የሮቤል ልጆች ...” (1 ዜና 5:1)
v    እስራኤል የእግዚአብሔር የበኩር ልጅ ተብሎ ተጠራ፥ “እስራኤል የበኵር ልጄ ነው ይገዛልኝ ዘንድ ልጄን ልቀቅ አልሁህ አንተም ትለቅቀው ዘንድ እንቢ አልህ እነሆ እኔ የበኵር  ልጅህን እገድላለሁ ትለዋለህ።” (ዘጸ 4:23) 
v    ንጉሥ ዳዊት ስለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በተናገረው ትንቢት በኩር ብሎ ጠርቶታል፥“እኔም ደግሞ በኵሬ አደርገዋለሁ፥ ከምድር ነገሥታትም ከፍ ይላል።” (መዝ 89:27)

No comments: