Tamar ~ ታማር፣ ትዕማር: “Tamar” means palm tree / SBD, (ዘፍ 38:8-30) ፥ (ሕዝ 47:19፣ 48:28)
The name ‘Tamar’ is derived from ‘Temr’ (ተምር) ፥ the meaning is ‘palm tree’ / Ibid.
The daughter-in-law of Judah, to whose eldest son, Er, she was married, “Then said Judah to Tamar his daughter in law ...” (Gen 38:8-30)
Other people with the same name are: Sister of Absalom, A daughter of David (1 Chr 3:9); A daughter of Absalom (2 Sam 14:27)
---------------------------------------------------------------------------------------------------
ታማር ~Tamar: ተምር፣ የተምር ዛፍ ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ትዕማር]

የቦታ ስም፥ “የደቡቡም ድንበር ከታማር ጀምሮ እስከ ...” (ሕዝ 47:19፣ 48:28)

ትዕማር ~Tamar: ትማር፣ ተማረ፣ ይቅር ተባለ፣ ምህረት አገኘ ማለት ነው ።
(‘ታምር ፥ ተምር፣ የተምር ዛፍ ማለት ነው’ ተብሎም ተተርጉሟል።)
[ተዛማጅ ስም- ታማር]
በዚህ ስም የሚታወቁ ሦስት ሰዎች አሉ።
1.                  የይሁዳም የበኵር ልጁ የዔር ሚስት፥ “ይሁዳም ለበኵር ልጁ ለዔር ትዕማር የምትባል ሚስት አጋባው” (ዘፍ 38:8-30)
2.                  የዳዊት ልጅ፣ የአቤሴሎም እኅት፥ “...ለዳዊት ልጅ ለአቤሴሎም አንዲት የተዋበች እኅት ነበረችው፥ ስምዋም ትዕማር ነበረ የዳዊትም ልጅ አምኖን ወደዳት።” (2 ሳሙ13:1-32)፣ (1 ዜና 3:9)
3.                  የአቤሴሎም ልጅ፥ “ለአቤሴሎምም ሦስት ወንዶች ልጆችና አንዲት ሴት ልጅ ተወለዱለት የሴቲቱም ልጅ ስም ትዕማር  ነበረ፥ እርስዋም የተዋበች ሴት ነበረች።” (2 ሳሙ 14:27)


No comments: