Nazareth ~ ናዝራዊ: netser, a "shoot" or "sprout." Some, however / EBD, ( 6:2-21)
The root word for Nazareth is ‘Ntsret’ (ንጽ) / Ibid.
....when either man or woman shall separate them selves to vow a vow of a Nazarite, to separate themselves unto the LORD” (Num 6:2-21)
----------------------------------------------------------------------------------------------------
ናዝራዊ ~Nazareth: ንጽት፣ ናጽራ ነጻ አነጣጣሪ፣ አስተዋይ፣ የወደፊቱን አርቆ የሚያይ፣ ብይ፣ ባህታዊ፣ መናኝ ማለት ነው።

ነጸረ ከሚለው ግስ የመጣ ስም ነው።

[ትርጉሙ የተቀደሰ ማለት ነው / መቅቃ]
ለእስራኤል ልጆች ንገራቸው። ሰው ወይም ሴት ለእግዚአብሔር ራሱን የተለየ ያደርግ ዘንድ ናዝራዊነት ስእለት ቢሳል፥” ( 6:2-21)
ናዝራዊነት መለያ ባሕርያት:-
·                     ከወይን ጠጅና ከሚያሰክር መጠጥ ራሱን የተለየ ያድርግ ከወይን ወይም ከሌላ ነገር የሚገኘውን ሆምጣጤ አይጠጣ፥ የወይንም ጭማቂ አይጠጣ የወይን እሸት ወይም ዘቢብ አይብላ።
·                     ራሱን ለመለየት ስእለት ባደረገበት ወራት ሁሉ በራሱ ላይ ምላጭ አይደርስም ለእግዚአብሔር የተለየበት ወራት እስኪፈጸም ድረስ የተቀደሰ ይሆናል፥ የራሱንም ጠጕር ያሳድጋል
·                     ለእግዚአብሔር ራሱን የተለየ ባደረገበት ወራት ሁሉ ወደ ሬሳ አይቅረብ።
·                     ለአምላኩ ያደረገው እስለት በራሱ ላይ ነውና አባቱ ወይም እናቱ ወይም ወንድሙ ወይም እኅቱ ሲሞቱ ሰውነቱን አያርክስባቸው።ራሱን የተለየ ባደረገበት ወራት ሁሉ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ነው
·                     ሰውም በአጠገቡ ድንገት ቢሞት የተለየውንም ራሱን ቢያረክስ፥ እርሱ በሚነጻበት ቀን ራሱን ይላጭ በሰባተኛው ቀን ይላጨው።
·                     ካህኑም አንዱን ለኃጢአት መሥዋዕት ሁለተኛውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርበዋል በሬሳም የተነሣ ኃጢአት ሠርቶአልና ያስተሰርይለታል፥ በዚያም ቀን ራሱን ይቀድሰዋል።
·                     ራሱን የተለየ ያደረገበትን ወራትም ለእግዚአብሔር ይቀድሳል፥ የአንድ ዓመትም ተባት ጠቦት ለበደ መሥዋዕት ያምጣ ናዝራዊነቱ ግን ረክሶአልና ያለፈው ወራት ሁሉ ከንቱ ይሆናል።


No comments: