Eleazar ~ አልዓዛር: “Eleazar” means help of God / SBD, (ዘጸ 6፡23)
The root words for ‘Eleazar’ are ‘El’ (ኤል) and ‘Zer’ (ዘር) ፥ The meaning is ‘one who related to the lord almighty’/ Ibid.
The third son of Aaron, “And Aaron took him Elisheba ... to wife; and she bares him Nadab, and Abihu, Eleazar, and Ithamar” (Ex 6:23)
Other people with the same name are: Third son of Aaron; after the death of Nadab and Abihu without children (Lev 10:6; Num 3:4); One of his first duties was in conjunction with Moses to superintend the census of the people (Num 6:3); The son of Abinadab, of the hill of Kirjath-jearim (1 Sam 7:1); A Merarite Levite, son of Mahli and grandson of Merari (1 Chr 23:21, 22; 24:28); A priest who took part in the Feast of Dedication under Nehemiah (Neh 12:42); One of the sons of Parosh, an Israelite (i.e. a layman) who had married a foreign wife (Ezr 10:25); Son of Phinehas, a Levit (Ezr 8:33); The son of Eliud, in the genealogy of Jesus Christ (Mat 1:15)
---------------------------------------------------------------------------------------------------
አልዓዛር ~Eleazar: ኤል አዛር፣ የጌታ ወገን፣ የተባረከ፣ የተቀደሰ፣ የአምላክ ወገን ማለት ነው። [ተዛማጅ ስሞች- አልዓዛር፣ ዓዛርኤል፣ ዓዛርኤል፣ አዛርኤል፣ ዓዛርኤል፣ ዓዝሪኤል፣ ዓዝርኤል፣ ኤሊዔዘር፣ ኤልዓዘር፣ አዛርኤል፣ ኤዝርኤል፣ ኤዝርኤል]

‘ኤል’ እና ‘ዘር’ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

[ትርጉሙ እግዚአብሔር እረዳቴ ነው ማለት ነው / መቅቃ]
በዚህ ስም የሚታወቁ አሥራ ሰባት ሰዎች አሉ።
I.                        አልዓዛር /Eleazar:
1.                  የነብዩ ሙሴ ወንድም፣ የአሮን ልጅ፥ (ዘጸ 6፡23)፣ (ዘኁ 3:4) ፣ (ዘኁ 26:3)
2.                  በኮረብታው ላይ የነበረው የአሚናዳብ ልጅ፥ (1 ሳሙ 7:1)
3.                  ከዳዊት ኃያላን ሰራዊት አንዱ፣ የዱዲ ልጅ፥ (2 ሳሙ 23:9፣ 1 ዜና 11:12) 
4.                  የሜራሪ ወገን፣ የሞሖሊና ልጅ፥ (1 ዜና 23:21 ፣ 22) ፣ (ሩት 24:28)
5.                  በነህምያ ዘመን የነበረ ካህን፥ (ነህ 12:42)
6.                  በባቢሎን በግዞት ዘመን፥ እንግዶች ሚስቶችን ካገቡ፥ (ዕዝ 10:25)
7.                  የፊንሐስ ልጅ አልዓዛር፥ (ዕዝ 8:33)
8.                  በጌታ የዘር ሐረግ የተገለጸው፣ የኤልዩድ ልጅ፥ (ማቴ 1:15)
II.                        አልዓዛር /Eliezar:         
1.                  የቢኒያም ወገን የቤኬር ልጅ፥ (1 ዜና 7:8)
2.                  የነብዩ ሙሴ ሁለተኛ ልጅ፥ (ዘጸ 18:4 ፣ 1 ዜና 23:15 ፣ 17 ፣ 26:25)
3.                  ዳዊት፥ የእስራኤል ሽማግሌዎችና፥ የሻለቆችም የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦት ከአቢዳራ ቤት ካመጡ ካህናት፥ (1 ዜና 15:24)
4.                  በእስራኤልም ነገዶች ላይ አለቃ የነበረ፥ የዝክሪ ልጅ አልዓዛር፥ (1 ዜና 27:16)
5.                  የመሪሳ ሰው የዶዳያ ልጅ አልዓዛር፥ (2 ዜና 20:37)
6.                  በንጉሡ በአርጤክስስ መንግሥት ከዕዝራ ጋር ከባቢሎን የወጡ የአባቶች ቤቶች አለቆች፥ (ዕዝ 8:16)፣
7.                  በዕዝራ ዘመን ከባቢሎን ሲወጡ እንግዳ ሚስቶችን ካገቡ፥ የኢያሱ ልጅ፥ (ዕዝ 10:18 ፣ 23 ፣ 31)
8.                  በጌታ የዘር ሐረግ የተጠቀሰው፣ የዮራም ልጅ፥ (ሉቃ 3:29)
·                     በአብርሃም ቤት አገልጋይ የነበረ የደማስቆ ሰው፥ “አብራምም፦ ... የቤቴም መጋቢ የደማስቆ ሰው ይህ ኤሊዔዘር ነው አለ።” (ዘፍ 15፡2፣3)
III.                        አልዓዛር /Lazarus: ለዘር
1.                  በሞተ በሦስተኛው ቀን ጌታ ያስነሳው፥ የማርያምና የማርታ ወንድም፥ (ኢያ 11:1)
2.                  በሰው ዘንድ የከበረ በእግዚአብሔር ፊት ርኵሰት መሆኑን ጌታ ሲያስተምራቸው የጠቀሰው፥ (ሉቃ 16:19-31)


No comments: