Jehoshua ~ ኢያሱ: “Jehoshua” means whose help is Jehovah; Help of Jehovah or savoiur / SBD, (ዘኁ 13፡16) ... [Related term(s):- Jeshua, Joshua, Jehoshuah]
The name ‘Jehoshua’ is derived from ‘Yah’ (ያህ) and ‘Shewa’ (ሽዋ) ፥ the meaning is ‘who gives life formthausands’ / Ibid.
See also:- Jehoshuah / ኢያሱ
The name of Joshua, “These are the names of the men which Moses sent to spy out the land; And Moses called Oshea the son of Nun Jehoshua,” In this form is given the name of Joshua in; (Num 13:16)
“None his son, Jehoshuah his son” (1 Chr 7:27)
---------------------------------------------------------------------------------------------------
ኢያሱ ~Hoshea, Jehoshua, Jeshua, Jesus, Joshua: ያህ ሽዋ፣ የሽዋስ፣ የሽዎች ጌታ፣ የብዙሃን አምላክ፣ የሽዎች አዳኝ፣ የብዙዎች ነጻነት ሰጭ ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ሆሴዕ፣ ኢየሱስ]

‘የሽህ’ እና ’ዋስ’ ከሚሉት ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።

[እግዚአብሔር ያድናል ፥ አዳኝ ማለት ነው / መቅቃ]
I.                        ኢያሱ /Hoshea:
1.                  የነዌ ልጅ፥ “ሙሴም የነዌም ልጅ ኢያሱ የዚህችን መዝሙር ቃሎች ሁሉ በሕዝቡ ጆሮ ተናገሩ።” (ዘዳ 32፡44)
2.                  የዓዛዝያ ልጅ፥ ሆሴዕ- (1 ዜና 27:20)
3.                  ከነህምያ ጋር የቃል ኪዳኑን ደብዳቤ ያተመ፥ ሆሴዕ- (ነህ 10:23)
II.                        ኢያሱ /Jehoshua: ከኤፍሬም ነገድ የሆነ፥ የነዌ ልጅ፥ “ምድሪቱን ይሰልሉ ዘንድ ሙሴ የላካቸው ሰዎች ስም ይህ ነው። ሙሴም የነዌን ልጅ አውሴን ኢያሱ ብሎ ጠራው” (ዘኁ  13፡16) ፣ (1 ዜና 7:27)
III.                        ኢያሱ /Jeshua:
1.                  ለዘጠነኛው ሊቀ ካህናት የነበረ፥ ኢያሱ፥ (ዕዝ2:36) ፣ (1 ዜና 24:11).
2.                  በንጉሡም በሕዝቅያስና በእግዚአብሔር ቤት አለቃ በዓዛርያስ ትእዛዝ፥ በካህናቱ ከተሞች በየሰሞናቸው ክፍላቸውን በእምነት ይሰጡ ከተመደቡ፥ (2 ዜና 31:15)
3.                  የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደ እየከተማቸው ከተመለሱት የአገር ልጆች፥ (ዕዝ 2:6፥ ዕዝ 7:11)
4.                  የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደ እየከተማቸው ከተመለሱት የአገር ልጆች፥ (ዕዝ 2:40፥ ነህ 7:43)
5.                  ሌዊያዊ፥ (ዕዝ 8:33)
6.                  ከባቢሎን መልስ የኢየሩሳሌምን ቅጥር ካደሱ፥ (ነህ 3:19)
7.                  ዕዝራ የእግዚአብሔር ማወቅ ሲያስተምር፥ የእግዚአብሔርን ሕግ መጽሐፍ ካአነበቡ፥ (ነህ 8:7፥ 9:4፣5)
8.                  የይሁዳ ከተማ፥ “በኢያሱ፥ በሞላዳ፥ በቤትጳሌጥ፥ በሐጸርሹዓል፥” (ነህ 11:26)
9.                  የቀድምኤልም ልጅ፥ (ነህ 12:24)
IV.                        ኢያሱ /Jesus:
1.                  ከሐዋርያው ጳውሎስ ጋር በጉዞው ላይ የነበረ፥ (ቆላ 4:11)
2.                  ከሙሴ በመቀጠል ሕዝበ እስራኤልን ወደ ቃልኪዳን አገራቸው የመራ፥ “ኢያሱ አሳርፎአቸው ኖሮ ቢሆንስ፥ ከዚያ በኋላ ስለ ሌላ ቀን ባልተናገረ ነበር።” (ዕብ 4:8)


No comments: