የግእዝ መዝገበ ቃላት
የአማርኛ መዝገበ ቃላት
የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
ENGLISH BIBLES
ENGLISH BIBLE DICTIONARIES
የአማርኛ መዝገበ ቃላት
የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
ENGLISH BIBLES
ENGLISH BIBLE DICTIONARIES
መግቢያ
ይህ መጽሐፍ፥ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላትን ምስጢራዊ ምንጭ መሠረት ያደረገ መዝገበ ቃላት ነው። ለእንግሊዘኛው ቅጅ ‘SABBATH’ የሚል ርዕስ ተሰጥቶታል። የአማረኛው ደግሞ ‘ቃለ አብ’ የሚለው ርዕስ ነው። ‘ቃለ አብ’ የሚለው ርዕስ የተሰጠው ስሙ ‘የእግዚአብሔር ቃል’ የሚለውን ሐሳብ የያዘ በመሆኑ ነው። ‘ቃለ አብ’ የሚለው ስም የተመሠረተው ‘ቃል’ እና ‘አብ’ ከሚሉ ሁለት ቃላት ነው። ‘ቃል’ ማለት በአንደበት የተነገረ፣ በጽሑፍ የሰፈረ ትርጉምና መልእክት ያዘለ ድምጽ፣ ንግግር፣ ህግ፣ ትእዛዝ፣ መመሪያ፣ ውል፣ ደንብ … ማለት ነው። ‘አብ’ ማለት ፈጣሪ፣ ወላጅ፣ መሪ፣ ታላቅ፣ አስተማሪ … ማለት ነው።
‘ቃለ አብ’ ተብሎ የተሰየመበት ሌላው ምክንያት ‘ቀለብ’ የሚለው ቃል የመጣው ‘ቃል’ እና ‘አብ’ ከሚሉት ቃላት ስለሆነ ነው። ‘የዕለት እንጀራችንን ዕለት ዕለት ስጠን፤” የሚለው ጸሎት ፥ የዕለት ‘ቀለብ’ን ከሚለው ሁኖ ምንጩ ደግሞ የዕለት ‘ቃለ አብ’ን … ነው። (ሉቃ 11:3)፥ እንዲሁም “አንተም የዘንዶውን ራሶች ቀጠቀጥህ ለኢትዮጵያ ሰዎችም ምግባቸውን ሰጠሃቸው።” የሚለው የመጣው ‘ቀለብን ሰጠሃቸው’ ከሚለው ሁኖ ምንጩ ደግሞ ‘ቃለ አብን’ ሰጠሃቸው የሚለው ነው። (መዝ 74:14)
እንግዲህ ‘ቃለአብ’ ማለት በእግዚአብሔር አብ የተፈጠረ፣ በአባቶች የተነገረ፣ በመጽሐፍ የሠፈረ፥ ህግ፣ ትዛዝ፣ መመሪያ፣ ውል፣ ደንብ ተብሎ ይተረጎማል። በጥቅሉ በመጽሐፉ ውስጥ የቀረቡ ቃላት በሙሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙትን ቃላት የያዘ በመሆኑ ‘ቃለአብ’ የሚል ርዕስ ተሰጠው።
“ምናልባት እየመረመሩ ያገኙት እንደሆነ እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩ የሰውን ወገኖች ሁሉ ከአንድ ፈጠረ፤ የተወሰኑትንም ዘመኖችና ለሚኖሩበትም ስፍራ መደበላቸው።ቢሆንም ከየአንዳንዳችን የራቀ አይደለም፥” (ሥራ 17፥ 20 እና 27)
‘እግዚአብሔርን መፈለግ’ በመንፈሳዊ ህይወት ለሚደረግ ጉዞ መነሻም ፥ መድረሻም ነው። የዚህ መዝገበ ቃላት አላማም እግዚአብሔር አስቀድሞ የወሰነውን፤ ለነቢያት የገለጠውን፤ በሐዋርያት የተላለፈውን፤ አባቶች ጠብቀው ያቆዩንን፥ ይህን ‘እግዚአብሔርን የመፈለግ ጥበብ’፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ፤ ለተተኪ ትውልድ ለማድረስ በሚደረገው ጥረት እገዛ ማድረግ ነው።
ትውልድ ሁሉ ከአባቶች የተረከበውንና በዘመኑ ያፈራውን ሀብት፣ ንብረት፥ ለተተኪው ትውልድ ማስተላለፍ፥ ከፍጥረት ቀን ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የቆየ ልማድ ነው። እንደ ዘመኑ ሁኔታ በዓይነትና በመጠን ቢለያይም ውርስ የሰውን ልጆች ሁሉ የማመሳሰል ባሕሪ አለው ። አባቶች ማውረስን ‘የውዴታ ግዴታችን ነው’ ብለው ስለሚያምኑ ለልጅ ልጅ ይተርፋል ያሉትን፤ በጉልበትቸው ያፈሩትን ሀብት፥ ንብረት ሁሉ ያከማቻሉ። በተለይ የቀደሙት አባቶች የሚያወርሱት ከቁሳዊ ንብረት ይልቅ መንፈሳዊ ጥበብን ነው። ከመንፈሳዊ ጥበባት ውስጥም ሃይማኖት ዋናው ጥሪት ሲሆን፥ ቋንቋ እና ታሪክ ደግሞ የውርሱ ሳጥን መክፈቻ ቁልፎች ሁነው ለትውልድ ሲተላለፉ ቆይተዋል።
‘ሃይማኖት’ የማይታይ ሀብትን በሚታየው ዓለም ስንኖር በእምነት ተቀብለን በሥርዓት የምንተዳደርበት መንግሥት ሲሆን፣ ታሪክ ደግሞ የዚያ የማይታየው መንግሥት ሀብት አንዱ ማረጋገጫ ነው። ምንም እንኳ ሃይማኖትን ከታሪክ፤ ታሪክን ከቋንቋ ለያይቶ ማጥናት ቢያዳግትም በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ግን ከሃይማኖትና ከታሪክ ይልቅ በቋንቋው ላይ ብቻ ትኩረት ለመስጠት ተሞክሯል።
‘ቋንቋ’ ቃላትን አግባብ ባለው መልኩ በማገናኘት መልእክትን ለማስተላለፍ ሲመሠረት፤ ቃላት ደግሞ ድምጽን በሥርዓት በማዋሐድ መልእክትን እንዲይዙ ሁነው ተፈጥረዋል። በአንድ ቋንቋ ውስጥ ያሉ ቃላትን ባሕሪ በመመርምር የድምጹን ምንጭ ማወቅ ሲቻል፤ የድምጹን ምንጭ በማጥናት ደግሞ የዚያን ድምጽ ባለቤት ሕብረተሰብ፣ ሃይማኖታዊ መልእክት እና ታሪካዊ አመጣጥ አጣርቶ ለመረዳት ይቻላል።
ይህን መዝገበ ቃላት የተለየ የሚያደርገው ፣ የጽሑፉ ጥናትና ያተኮረባቸው ቃላት በሙሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙትን ብቻ መሠረት ማድረጉ ነው። ይህም ማለት በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ያሉ ቃላትን በማንኛውም ቋንቋ በተጻፈ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ ሁኖ በልዩ ልዩ ፊደላት ወይም አልፋቤት ቢጻፉም ቃላቱ የሚሰጡት ድምጽና ትርጉም ግን አንድ ነው። ለማመሳከር እንዲረዳ በላቲን ፊደላት የተጻፈን የእንግሊዝ አገርን ቋንቋ ከአማርኛው ጋር በማመሳከር ተዘጋጅቷል። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉትን ቃላት ሥርዓት በመመርመር እና በማነጻጸር የቋንቋውን ምንጭና ምስጢራዊ ትርጉም ለማሳየት ተሞክሯል። የዚህ ጽሑፍ መነሻ ምክንያትም ይህን እውነት ለማብራራት ነው። ‘እውነትን ብታውቅ እውነት ነጻ ታወጣሃለች’ እንዲል፤ ኃይማኖትም እውነትን መፈለግ፣ እውነትን ማግኘትና በእውነት መኖር ነው።
ይህ ቃል አማረኛ ነው፥ ያኛው ደግሞ ግእዝ፥ ይህኛው ትግረኛ፥ ያኛው ጉራገኛ ወዘተረፈ፥ በሚል ውዝግብ የሚባክነውን ጊዜ ለማትረፍ መፍትሄ ይሆናል በማለት ‘ETHIOPISH’ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል።
ይህን አባባል የበለጠ እንዲያጎላ፥ የሚከተለውን ግጥም (ከአለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ የግእዝ መዝገበ ቃላት መግቢያ የተወሰደ) ይመልከቱ።
"ቋንቆቻችንም፥ባልና፡ሚስት፥
ርስ፡በርሳቸው፡የሚፋቱት፥
ላይለያዩ፡ተለያይተው፥
ላይለያዩ፡ተለያይተው፥
ያሟግቱናል፡ኹለት፡መስለው።
ከቶ፡እኛ፡አንችልም፡ልንለያቸው፤
ከቶ፡እኛ፡አንችልም፡ልንለያቸው፤
እግዜር፡ነውና፡ያጣመራቸው።
ነፍስና፡ሥጋ፡ከተለያዩ፥
ነፍስና፡ሥጋ፡ከተለያዩ፥
ሕያው፡እንዳይኾን፡የሰው፡ባሕርዩ፥
ያማርኛም፡ቃል፥የግእዝ፡ሥጋ፥
ያማርኛም፡ቃል፥የግእዝ፡ሥጋ፥
አለግእዝ፡ነፍስ፥ሬሳ፡ባልጋ።
ሬሳውን፡ቃል፡የሚሸከሙ፥
በግእዝ፡ቋንቋ፡ሲፈታ፡ይስሙ።" ኪ ወ ክ / አ
ሬሳውን፡ቃል፡የሚሸከሙ፥
በግእዝ፡ቋንቋ፡ሲፈታ፡ይስሙ።" ኪ ወ ክ / አ
የመጽሐፉን ጠቅላላ ይዘት በአጭሩ ለመገንዘብ ከዚህ ቀጥሎ የቀረቡትን ሁለት ቃላት ማየት ይጠቅማል።
ቁሚ ~ Cumi: ቁሚ፣ ቆመ፣ መቆም፣ መነሳት፣ መጽናት፣ አለመቀመጥ፣ አለመተኛት…ማለት ነው።
ጌታ የሞተችውን ልጅ ሲያድን የተናገረው ቃል፥ “የብላቴናይቱንም እጅ ይዞ። ጣሊታ ቁሚ አላት፤ ፍችውም አንቺ ብላቴና ተነሽ እልሻለሁ ነው።” (ማር 5፡41)
Cumi ~ ቁሚ: Arise / SBD
Cumi ~ ቁሚ: Arise / SBD
“And he took the damsel by the hand, and said unto her, Talitha cumi; which is, being interpreted, Damsel, I say unto thee, arise.” (Mar 5:41)
[‘ቁሚ’ የሚለው ቃል በእንግሊዘኛው መጽሐፍ ቅዱስ ‘cumi’ ተብሎ መጻፉን ልብ ሊሉ ይገባል።]
ይስሐቅ ~ Isaac: ይሳቅ፣ ይስሐቅ፣ መሳቅ፣ ፈገግታ ማሳየት፣ ጥርስን በደስታ መግለጥ… ማለት ነው።
[ትርጉሙ “ይስቃል” ማለት ነው / መቅቃ]
ይስሐቅ ~ Isaac: ይሳቅ፣ ይስሐቅ፣ መሳቅ፣ ፈገግታ ማሳየት፣ ጥርስን በደስታ መግለጥ… ማለት ነው።
[ትርጉሙ “ይስቃል” ማለት ነው / መቅቃ]
ሣራ ለአብርሃም የወለደችለት ልጅ፥ “አብርሃምም የተወለደለትን ሣራ የወለደችለትን የልጁን ስም ይስሐቅ ብሎ ጠራው።” (ዘፍ 21፡1-3) “ሣራም፦ እግዚአብሔር ሳቅ አድርጎልኛል ይህንንም የሚሰማ ሁሉ በእኔ ምክንያት ይስቃል አለች።” (ዘፍ 21፡6)
Isaac ~ ይስሐቅ: Laughter / EBD
Isaac ~ ይስሐቅ: Laughter / EBD
The son whom Sara bore to Abraham, in the hundredth year of his age, at Gerar; “And God said Sarah thy wife shall bear thee a son indeed; and thou shalt call his name Isaac: ... (Gen 21:1-3); “And Sarah said, God hath made me to laugh, so that all that hear will laugh with me” (Gen 21፡6)
This is an ‘Amharic- English bible dictionary’. The dictionary contains over a thousand words, exclusively from the bible. Since it is an introductory version, it is limited to the very key words and their exceptional meanings.
The dictionary is based on a search on the origins and secret massages of spiritual language.
Thus, as an outline it may help you to pay attention that…
The English word ‘the’ has the same meaning as the Ethiopish ‘ዘ’, which is an article, like the (ዘ ) Ethiopia, አቡነ ‘ዘ’ በሰማያት፣ ‘ዘ’ ደብረ ሊባኖስ etc;
Words like ‘Alphabet ~ አልፋቤት, Ambassador ~ አምባሳዳር, Feastival ~ ፌስታ በዓል and so on’ are originated from the Ethiopish language.
The English word ‘mystery’ and the Ethiopish ‘mist.ir’ (ምስጢር) have the same meaning- secrete.
The name ‘Andréa’s’ and the word ‘enderasie’ (እንደ ራሴ) have the same meaning-‘manly’.
Most biblical names, like ‘Abimelik ~ አባ መላክ፣ Ebenezer ~ አብነ ዘር፣ Elisabeth ~ ኤል ሰባት፣ Emmanuel ~አማነ ኤል፣ Gabriel ~ ገብረ ኤል፣ Israel ~ (እ) ሥራ ኤል፣ Melkisadic ~ መልከ ጸዴቅ and so on’ are Ethiopish rooted.
The English word ‘call’ is derived from the Ethiopish ‘Qal’ (ቃል) meaning voice.
The name ‘Simon’ is from the word ‘smane’ (ስማነ) meaning hears me, listen…
The word ‘Amen’ is from the word, Aman (አምን); the meaning is faithful and peaceful unity.
The word ‘wine’ came from the Ethiopish word ‘Weyn’ (ወይን), an alcoholic drink.
The name ‘Zechariah’ derived from the words ‘Zkre’ (ዝክረ) and ‘yah’ (ያህ), meaning remembrance of Jehovah. And so on…
© 2004/2012 www.ethiopish.net
Alem Publishers
1(646) 420 3665